የ Radio D ዝግጅት ክፍል ሰራተኞች ስለ ካርኔቫል ያላቸው አመለካከት የተለየ ነው። ኮምፑ እንዲያፈላልግ የተሰጠው ትዕዛዝ ሁለቱን ጋዜጠኞች የካርኔቫልን በዐል ወደሚያደንቁት እሽቫርስቫልድ ቦታ ያመራቸዋል። ግን ይኼ ለሁሉም ተካፋዮች አስደሳች አይሆንም።
ካርኔቫል በአንዳንድ የጀርመን አካባቢዎች በደንብ ይከበራል። በባህላዊው ሮዝን ሞንታግ ተብሎ በሚጠራው ሰኞ ቀን ቢሮ ውስጥ በበዐሉ የተነሳ ብዙ አለመግባባት ተፈጠረ። ፓውላ ፊሊፕ የጠንቋይ ልብስ መልበሱን አልተቀበለችውም። ልብሱ የመጨረሻ አስቀያሚ ነው ትላለች።
ፊሊፕ ጥናት ለማድረግ ወደ እሽቫርስቫልድ ወደሚባ ... Show More