ፊሊፕ ፋታ ሊያገኝ አልቻለም። የሚናከሱ ነፍሳቶች ሰላም አልሰጥ ማለታቸው ሳያንስ የጎረቤት ጫጫታ አላስቀምጥ ብሎታል። ያልተጠበቀ ስልክ ደሞ ከበርሊን ይደወልለትና በፍጥነት ወደ Radio D ጉዞ ይጀምራል።
ፊሊፕ ወደ ክፍለ ሀገር ሄዶ እንደጠበቀው እንዲዝናና ማንም የተመኘለት ያለ አይመስልም። አንድ ክብ መጋዝና አንድ ጥሩ ዋሽንት መጫወት የማይችል ሰውዬ ብስጭት ያደርጉታል። በዚህ አጋጣሚ በርሊን Radio D ከምትሰራው ፓውላ የመጣው የስልክ ጥሪ በሰአቱ ነበር። ፊሊፕ ሱሪ ባንገት ብሎ እናቱን አስቀይሞ ወደ ዋና ከተማው ይመጣል።
እዚህ ጋም በጥቂት ቃላቶች አማካ ... Show More