"አውስትራሊያ ጥሩ ሀገር ናት፣ ብንመጣም የምናተርፍባት እንጂ የምታከስረን ሀገር አይደለችም፤ ሕዝቧም ተቀባይ የሆነ ሀገር ስለሆነች ወደ አውስትራሊያ መብረር የማይፈልግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ የለም። እርግጠኛ ነኝ፤ አውሮፕላን እንደተገኘ የድርጅቴ ቀዳሚ ጉዳይ የሚሆነው ወደ አውስትራሊያ መብረር ነው" ያሉት ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ፤ ተሰናባች የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላናድ ቀጣና ሥራ አስኪያጅ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድን የቀጣና ተግዳሮቶችንና ስኬታማ ክንውኖችን አንስተው ይናገራሉ።