የአቶ ብዙአየነህ ኃይለማርያም ይፍጠር ድንገተኛ ሕልፈተ ሕይወት ከቤተሰብ እስከ ማኅበረሰብ አባላት ብርቱ ሐዘንን ፈጥሯል። ሕልፈታቸውንም ተከትሎ አብሮ አደጋቸው አቶ ኬኔዲ ገብረየሱስ "ብዙአየነህ በማኅበረሰቡ ውስጥ ጥሩ ስም ነበረው። ሕልፈቱ በጣም የሚያስደነግጥ፤ በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ማኅበረሰቡ ይጎዳል" ሲሉ፤ የረጅም ጊዜ ወዳጃቸው አቶ ልዑል ፍስሃ "ብዙአየነህ ላመነበት ነገር በትጋት የሚሠራ፤ ለዕውቀት ከፍተኛ ቦታ የሚሰጥ፤ ትልቅ ሰው ነበር። ሐዘናችን ጥልቅ ነው" ብለዋል። የአቶ ብዙአየነህ ፀሎተ ፍትሐት ሐሙስ ግንቦት 21 ቀን 2017 / ሜይ 29 ቀን 2025 ... Show More