"ለማ ክብረት በዓለም ላይ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሊሰኝ የሚችል፤ ቅን፣ ሰው አክባሪና የታመመን ጠያቂ ነው" የሚሉት የቀድሞው የለማ ክብረት የብሔራዊ ቡድን ባልደረባ አቶ ኤርሚያስ ወንድሙና "ለሀገራቸው ያገለገሉ የማኅበረሰብ አባላትን ዕውቅንና ከበሬታ ልንቸራቸው ይገባል" የሚሉት በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ ቅዳሜ ሰኔ 1 / ጁን 8 በሜልበር ስለሚካሔደው የሕይወት ዘመን አገልግሎት ልዩ የዕውቅና ፕሮግራም ያስረዳሉ፤ የግብዣ ጥሪና ምስጋናም ለማኅበረሰብ አባላት ያስተላልፋሉ።